B1 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
1. በገና ምንድን ነዉ?
በገና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከምንገለገልባቸዉ ንዋየ ቅድሳት ዉስጥ የዜማ መሳሪያ ከሆኑት መካከል አንዱ ነዉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ የዜማ መሣሪያዎች መሠረታቸዉ መጽሐፍ ቅዱስ ነዉ፡፡ ለምሳሌ በገና፣ መሰንቆ፣ ጸናጽል፣ መለከት … በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ብዙ ጊዜ እስከ አገልግሎታቸዉ ተጠቅሰዉ ይገኛል፡፡
1ኛ ዜና 15÷16 ‹‹ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ ድምጻቸዉንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንደሞቻቸዉን ይሾሙ ዘንድ ለሌዋዊያን አለቆች ተናገረ›› ከዚህ ቃል የምንረዳዉ ከዜማ መሳሪያዎች ዉስጥ አንዱ በገና መሆኑን ነዉ፡፡ ምዕመናን በተለያዩ ዘመናት ሲገለገሉበትና ባለፉት አመታት ዉስጥ ደግሞ የጠፋ ሲመስል ቢቆይም አሁን ባለንበት ጊዜ በስፋት በተለያየ መንገድ እየተገለገልንበት ይገኛል፡፡
1ኛ ዜና 15
o በዚያን ጊዜም ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ይሸከሙ ዘንድ፤ ለዘላለሙም ያገለግሉት ዘንድ እግዚአብሔር ከመረጣቸዉ ከሌዋዉያን በቀር ማንም የእግዚአብሔርን ታቦት ይሸከም ዘንድ አይገባዉም አለ፡፡
o ዳዊትም ወዳዘጋጀለት ቦታ የእግዚአብሔርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስራኤልን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ፡፡
o እናንተ የሌዋዉያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናችሁ ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ ታመጡ ዘንድ እናንተና ወንድሞቻችሁ ተቀደሱ፡፡
o ቀድሞም አልተሸከማችሁምና፤ እንደ ሥርዓቱም አልፈለግነዉምና አመላካችን እግዚአብሔር ስብራት አደረገ አላቸዉ፡፡
o የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ያመጡ ዘንድ ካህናቱና ሌዋዉያኑ ተቀደሱ፡፡
o ሙሴም እንዳዘዘዉ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሌዋዉያን ልጆች የእግዚአብሔርን ታቦት በትከሻቸዉ ላይ በመሎጊያዎቹ ተሸከሙ፡፡
o ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ ድምጻቸዉንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንደሞቻቸዉን ይሾሙ ዘንድ ለሌዋዊያን አለቆች ተናገረ
o መዘምራንም ኤማንና አሳፍ ኤታንም በናስ ጸናጽል ከፍ አድርገዉ ያሰሙ ነበረ
o ዘካርያስ፡ዓዝዔል፡ሰሚራሞት፡ይሒኤል፡ዑኒ፡ኤልያብ፡ መዕሤያ በናያስ በመሰንቆ ምሥጢር ነገር ያዜሙ ነበር፡፡
o መቲትያ፡ ኤልፍሌሁ፡ ሚቅኒያ፡ ዖሌድኤዶም፡ ይዒኤል፡ ዓዛዚያ፡ ስምንት አዉታር ባለዉ በገና ይዘምሩ ነበረ::
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ