B2 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
1.1.
በቤተ ክርስቲያን የሚገኙት ንዋየ ቅድሳት ምን ምን ናቸዉ?
ንዋየ ቅድሳት የሚለዉ ሐረግ የሁለት ቃል ጥምር ነዉ፡፡
1. ንዋይ
ንዋይ ማለት ገንዘብ ፤ ጥሪት ፤ ቅርስ ፤ / ወርቅ ፤ብር ፤ ከብት …/ ይህም ማለት ከሳር ፤ ከእንጨት
፤ ከማእድን ፤ ከብረት ፤ ከጭቃ ፤ ከቁርበት ሌላም ሁሉ መልክና ቅርጽ ጌጥም ኖሮት የሚዘጋጅ ነው ፡፡ ወይም እንዲሁ በራሱ ጥሬ
ዕቃ ከንብረት ይቆጠራልና ይህም ንዋይ ይባላል፡፡
2. ቅድሳት
ቅድሳት ማለት ደግሞ ቅድስና ክብር ንጹህ ጸጋ ያላቸው የእግዚብሔር የሆኑ ለእግዚብሔር አገልግሎት የተለያዩ ማለት ነው
፡፡ ? ‹‹ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን
ይቀጣናል ›› ዕብ 12፤10
ንዋየ ቅድሳት
ከተመረጡ ከተለያዩ የተለየ ለዘለዓለም ስሙ የሚኖርበት ምርጥ እቃ ማለት
ነው ፡፡ይህም ስለሆነ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ተባርኮና ተጸልዮበት ነዉ የሚገባው ፤ ከቡራኬ በኋላ ግን ተራ እቃ የነበረው ንዋየ
ቅድሳት ሆኖ ለቤተመቅደስ የአምልኮ ሥርዓት መፈጸሚያ የክብር ዕቃ
በመሆኑ በማንም የማይነካ ይሆናል፡፡
‹‹ በተቀደሱት በንዋይ ቅድሳቱ ቤተመዛግብቱ ሁሉ ላይ ተሹመው ነበር ›› 1ኛ ዜና 26፤26 ‹‹ደግሞም ለእግዚአብሔር
ቤት አደባባዮችና በዙሪያቸው ለሚሆኑ ጓዳዎች ለእግዚአብሔር የሚሆኑ ቤተ መዛግብት በመንፈሱ ላሰበው ሁሉ ምሳሌን ሰጠው ›› 1ኛ
ዜና 28፤12
ንዋየ ቅድሳት በአጠቃላይ ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች የሚጠሩበት ስም ነው፡፡ እነዚህንም በሶስት ክፍሎች
ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡
አገልግሎት ሰጭ ንዋያተ ቅድሳት
ሰንና ብርት፣ ሜሮን፣ ቀንዲል/ቅብኣ ቅዱስ/፣ ዕጣን፣ ጽንሐሕ፣ ሙዳይ፣ ጧፍና ሻማ፣ መቅረዝ፣ መኮስተሪያ፣ አትሮንስ፣
ሙዳየ ምጽዋት፣ ቃጭል፣ ደወል፣ መቋሚያ
አልባሳት (ልብሰ ተክህኖ)
የቀሳዉስት ቀሚስ፣ ካባ፣ የቄስ ሞጣሕት፣ ቆብ፣ ጥምጥም፣ ማክበሪያ፣ ፈረጅያ፣ የዲያቆን ቀሚስ፣ ለምድ፣ የዲያቆን ሞጣሕት፣
አክሊል፣ ልብሰ ታቦት፣ መጎናጸፊያ፣ ቀጸላ፣ መጋረጃ፣ ምንጣፍ፣ ድባብ(ጥላ)፣ ግምጃ፣ ማህደር
የዜማ ዕቃዎች
ዜማ ማለት ስልት ያለዉ ጩኸት ማለት ሲሆን ድምጽ እና የሰዎች ድምጽ በሶስት ይመደባል ግዕዝ ዕዝል አራራይ ይባላሉ፡፡
እነዚህ የዜማ ዕቃዎች በሶስት ይከፈላሉ፤
o
በእጅ የሚደረደሩ የሚከረከሩ /በገና ፡ መሰንቆ/
o
የሚነፉ /መለከት ፡ እምቢልታ ፡ ዋሽንት/
o
ዕቃዎቹን እርስበርስ በማማታትና በእጅ በመምታት /ከበሮ ፡ አታሞ ፡ ነጋሪት ፡ ጸናጽል/
o
መቋሚያ ፦ይህም ሁለት ጥቅሞች አሉት፡፡ለዝማሜና ለምርኩዝነት ወይም ለድጋፍ ያገለግላል፡፡ እንደ ዜማ
መሣሪያ የሚያገለግለዉ ለዝማሜ ሲዉል ብቻ ነዉ፡፡ ይህም ከመሬት ጋር በሚጋጭበት ጊዜ ድምፅ ስለሚያወጣ ነዉ፡፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ