ልጥፎች

ከጃንዋሪ, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ
               መሰንቆ መሰንቆ አንድ ምሰሶና አንድ ክር ያለዉ የዜማ ዕቃ ነዉ፡፡ ክሩ ከፈረስ ጭራ ይዘጋጃል በአንድነት የሚወጠረዉ ክር ብዛቱ ቢያንስ 40 ቢበዛ 80 ይሆናል፡፡ ምሥጢር o    አ ንድ ምሰሶዉ ፡ አንድ ሐይማኖት o    አንድ ወራጅ ክሩ ፡ አንዲት ጥምቀት o    40 እና 80 ክር መሆኑ ፡ የወንድና ሴት ጥምቀት o    ዕጣኑ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ o    ክሩ በዕጣን መቀባቱ ፡ የመንፈስ ቅዱስ ልጅነት o    መሰንቆ 5 ያህል መስቀል ይታይበታል ·        የምሰሶ አናት ላይ ·        መቃኛዉ ከምሰሶ ጋር ሲተያይ ·        የመሰንቆ ሳጥን ቅርጽ ·        የክር መወጠሪያ በርኩማ ከክር ጋር ተመሳቅሎ ·        መከርከሪያዉ በመሰንቆ ክር ጋር አልፎ ሲከረከር ሲታይ፤ አምስቱ መስቀል ማታየቱ አምስቱ ቅንዋተ መስቀል ምሳሌ ናቸዉ፡፡
  B1                            በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 1.                                                           በገና  ምንድን ነዉ? በገና በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ  ቤተ ክርስቲያን ከምንገለገልባቸ ዉ   ንዋየ ቅድሳት ዉስጥ የዜማ መሳሪያ ከሆኑት መካከል አንዱ  ነዉ፡፡  በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ የዜማ መሣሪያዎች መሠረታቸዉ መጽሐፍ ቅዱስ ነዉ፡፡ ለምሳሌ በገና፣ መሰንቆ፣ ጸናጽል፣ መለከት … በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ብዙ ጊዜ እስከ አገልግሎታቸዉ ተጠቅሰዉ ይገኛል፡፡    1ኛ ዜና 15÷16 ‹‹ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ ድምጻቸዉንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንደሞቻቸዉን ይሾሙ ዘንድ ለሌዋዊያን አለቆች ተናገረ›› ከዚህ ቃል የምንረዳዉ ከዜማ መሳሪያዎች ዉስጥ አንዱ በገና መሆኑን ነዉ፡፡ ምዕመናን በተለያዩ ዘመናት ሲገለገሉበትና ባለፉት አመታት ዉስጥ ደግሞ የጠፋ ሲመስል ቢቆይም አሁን ባለንበት ጊዜ በስፋት በተለያየ መንገድ እየተገለገልንበት ይገኛል፡፡ 1ኛ ዜና 15 o     ለእግዚአብሔር ታቦት ስፍራ አዘጋጀ፤ ድንኳን ተከለለት o     በዚያን ጊ...
B2           በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 1.1.          በቤተ ክርስቲያን የሚገኙት ንዋየ ቅድሳት ምን ምን ናቸዉ? ንዋየ ቅድሳት የሚለዉ ሐረግ የሁለት ቃል ጥምር ነዉ፡፡ 1.      ንዋይ ንዋይ ማለት ገንዘብ ፤ ጥሪት ፤ ቅርስ ፤ / ወርቅ ፤ብር ፤ ከብት …/ ይህም ማለት ከሳር ፤ ከእንጨት ፤ ከማእድን ፤ ከብረት ፤ ከጭቃ ፤ ከቁርበት ሌላም ሁሉ መልክና ቅርጽ ጌጥም ኖሮት የሚዘጋጅ ነው ፡፡ ወይም እንዲሁ በራሱ ጥሬ ዕቃ ከንብረት ይቆጠራልና ይህም ንዋይ ይባላል፡፡ 2.     ቅድሳት ቅድሳት ማለት ደግሞ ቅድስና ክብር ንጹህ ጸጋ ያላቸው የእግዚብሔር የሆኑ ለእግዚብሔር አገልግሎት የተለያዩ ማለት ነው ፡፡ ? ‹‹ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል ›› ዕብ 12፤10 ንዋየ ቅድሳት ከተመረጡ ከተለያዩ የተለየ ለዘለዓለም ስሙ የሚኖርበት ምርጥ እቃ ማለት ነው ፡፡ይህም ስለሆነ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ተባርኮና ተጸልዮበት ነዉ የሚገባው ፤ ከቡራኬ በኋላ ግን ተራ እቃ የነበረው ንዋየ ቅድሳት ሆኖ ለቤተመቅደስ የአምልኮ ሥርዓት መፈጸሚያ የክብር ዕቃ  በመሆኑ በማንም የማይነካ ይሆናል፡፡ ‹‹ በተቀደሱት በንዋይ ቅድሳቱ ቤተመዛግብቱ ሁሉ ላይ ተሹመው ነበር ›› 1ኛ ዜና 26፤26 ‹‹ደግሞም ለእግዚአብሔር ቤት አደባባዮችና በዙሪያቸው ለሚሆኑ ጓዳዎች ለእግዚአብሔር የሚሆኑ ቤተ መዛግብት በመንፈሱ ላሰበው ሁሉ ምሳሌን ሰጠው ›› 1ኛ ዜና 28፤12 ንዋየ ቅድሳት በአጠቃላይ ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉ ...